Tuesday, June 12, 2012

የሰኔ ፆም እና በረከቱ

 from  facebook Mesfin Haile

አንዳንዶች የሰኔ ፆም የቄስ ፆም ነው በሚል ከመፆም ወደኋላ ሲሉ ይታያሉ ነገር ግን ቅድስት ቤተክርስትያን በአዋጅ ከምትፆቸው ሰባት አፅዋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ክርስትያን ቢፆመው እጅግ በርካታ በረከቶችን ያገኝበታል ከነዚህም ጥቂቶችን እነሆ

1. በረከተ ሐዋርያት ይገኝበታል ይህን ፆም መጀመርያ ፆመው እንድፆመው ስርአት የሰሩልን ሐዋርያት ናቸው ሰለዚህም ፆፆሙ መታሰቢያነቱ የሐዋርያት ነው የጻድቅ መታሰቢያ ደግሞ ለበረከት ነው ምሳ 10 ፡7 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም የሐዋርያቱን በረከት እናገኛለን ሐዋ 13 ፡1-3 ሐዋ 14 ፡23

2. በስራችንና በአገልግሎታችን በረከት እናገኛለን ሐዋርያት ይህን ፆም የፆሙት አገልግሎታቸው እነዲከናወንላቸው እነዲባረክላቸው ነው ነብዩ ነህምያም እየሩሳሌምን የመስራት ተግባሩ እነዲባረክለት በፆመው ፆም ስራው ሁሉ ተባርኮለታል ነህም 1 ፡4 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም በዕለት ተዕለት ተግባራትን በረከት እናገናለን
 


3. ዝናመ ምህረትን ጠለ በረከትን እናገኛለን የሰኔ ፆም በአገራችን የክረምቱ መግቢያ ላይ የሚፆም ፆም ነው ይህም መጪው የክረምቱ ወራት የተስተካከለ የምህረት ዝናም እነዲኖረው ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል ዘመን ዝናም ጠፍቶ ዛፎቹ ሳይቀር በደረቁ ጊዜ በፆም በጸሎት ወደ እግዚአብሄር በተማጸኑ ሰአት ዝናመ በረከትነ አግኝተዋል ኢዩ 1 ፡12-14
 

4. በረከተ ምርትን እናገኛለን የሰኔ ፆም በሃገራችን ገበሬው ዘር መዝራት በሚጀምርበት ጊዜ የሚፆም ፆም ነው ስለዚህም በዚህ ሰአት የሚፆመው ፆም ዘርን እነዲባረክ በረከት እነዲበዛ ያደርጋል ይህም አገር ወገን ከረሃብ ከችግር ነፃ እነዲወጣ ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል እነደትገለጸው በፆም የዕህል የመጠጥ በረከት ይገኛል ኢዩ 2 ፡12-14
 

5. የነፍስ በረከትን እናገኛለን ፆም በመንፈስ የደከመች የዛለች ነፍስን ያበረታል የነፍስን ቁስል ይፈውሳል ስጋዊ ኃይልን ያደክማል የስጋን ፈቃድ ለነፍስ ያስገዛል መዝ 108 ፡24, ገላ5 ፡24, የአለምን ሃሳብ ያስወግዳል ከእግዚአብሄር ያስታርቃል ሮሜ 8 ፡7, ዮናስ 3 ፡1-10, አጋንንትን ያርቃል ማቴ 17 ፡21 ሚስጢር ይገልጣል ዘስ 34 ፡27-28, ዳን10 ፡1-3
« በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ ከርሱም የቀናውን መንገድ ለእናና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ
እንለምን ዘንድ………… ፆምን አወጅሁ » መስሐፈ ዕዝራ 8 ፡21
ከመዋዕለ ፆሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን

1 comment:

  1. እጥር ምጥን ያለ ቆንጆ ጽሁፍ፡ ከሐዋርያት ረድኤት ከጾሙ በረከት ያሳትፈን!

    ReplyDelete