ስታመምም ታሞ
በችግሬ ደርሶ
ሳለቅስ አልቅሶ
የእርሱን ነገር ትቶ
ስለእኔ ተሟግቶ
ሲከፋኝ ለምኖ
ፈጣሪን ተማጽኖ
ከውድቀቴ አንስቶ
ድካሜን ተጋርቶ ምላሹን ሳይቆጥር
ሊረዳኝ የሚጥር።
ሁሌም የማገኘው።
ዘይቱን አፍሶ
ቁስለቴን ፈውሶ።ነፍሴን በነፍሱ አስሮ
በእኔነቴ አክብሮ።
ከልቡ የሚወደኝ
በቃሉም የሚገኝ።
የልብ ባልንጀራ
አንተን የሚፈራ።
መገኛው ከአንተ ነው
የእኛስ መላም የለው።
ስለዚህ አምላኬ
እኔንም አጽንተህ
እንደ ዳዊት አርገህ
የሚወደኝን ሰው
ዮናታን አምጥተህ
በሰላም በጤና
ውለህ እንዳሳደርከኝ
አንተን የሚመስል
ባልንጀራን ስጠኝ።
ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን
ጥቅምት 7/2003 ዓም oct 17/2010
/ዋሽንግተን ዲሲ/
ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን
ጥቅምት 7/2003 ዓም oct 17/2010
/ዋሽንግተን ዲሲ/
Tuesday, October 19, 2010
http://www.melakuezezew.info/2011/07/blog-post.html
ቀን ያለው ቀን ሰጠኝ
ቤተ ጳውሎስ፤ ሚያዚያ 9 2004 ዓ.ም.
ገድሎ ማዳን ሳይሆን ፣ ሞቶ ማዳን ማለት
ምን ዓይነት ስሌት ነው ፣ ምን ዓይነት ጀግንነት?
ተወልዶ ያደገው ፣ በመስቀል የሞተው ፣ ደግሞም የተነሳው
የማዳን ክዋኔው ፣ ጥበቡ ስውር ነው ምሥጢሩም ጥልቅ ነው
ስለፈሩት አይደል ፣ ወይ ስለተወደደ
ስለ ፍቅር ብሎ ፣ ከሰማይ ወረደ
ነጻነት ለማወጅ ፣ በራሱም ፈረደ
ሰው ሆነና ሞተ ፣ ለጥቆም ተነሳ የሚለው ቃላችን
መሠረቱ ይኸ ነው ፣ ድኅነተ እምነት ፣ በክርስትናችን
አምላክ የወደደን እኛ ስንከዳው
ይህን ያስፈጸመው ፣ ምክንያቱ ምንድነው?
ይህን ሊንክ ባንጠቀመው ጥሩ ነው ወንደሜ! ቤተ ጳውሎስ የምንፍቅና እንክርዳድ ያለበት ድር ነው
ReplyDelete