Friday, May 18, 2012

ቅዱስ ያሬድ ማነው?

ልዩ መርሐ ግብር ከግንቦት 10 እስከ 12

መንፈሳዊ ጌሞች እንዲሠሩ ይፈለጋል




  Wendemsesha Ayele Kesis 

ከወራት በፊት ባስተዋውቅም ምላሽ ያላገኘሁበት ግብዣ ስለነበረኝ ዛሬም በድጋሚ ጋብዣችኋለሁ።

አዲስ አድማስ ጋዜጣ በታህሣስ ፴ እትሙ ኮምፒውተር የኢትዮጵያውያን የሂሳብ ቀመር ሊቃውንት ውጤት ነው ብሎ ቢቢሲን ጠቅሶ አስገርሞኛል፤ የሊቃውንቱ የስሌት ዘዴ /ማባዛት፣ ማካፈል/መግደፍ፣ ወዘተ/ ከኮምፒውተር ሌላ የካሽ ሬጅስተርና መሰል ማሽኖችን አሠራር ለመፈልሰፍ መነሻ ስለሆነ የኢትዮጵያውያን ፈጠራ ነው ብሎ ፈርዷል፤ ፓተንቱ ባይሰጠንም /ያው እንደሀገርም እንደሊቃውንቱ ዝምድናም ለቤ/ክ ልጆች ይገባናልና/ ኮርቻለሁ።
ሌላው የዛሬው ዘገባዬ ደግሞ መንፈሳዊ ጥቅም ያላቸው መዝናኛ ጨዋታዎች /ጌሞች/ ሊዘጋጁ እንደሆነ ያረጋግጣል።
እስካሁን በብዛት የተዘጋጁት ጌሞች በመድፍ ተኩሶ በገደሉት ብዛት፣ ያገኙትን ለመብላትና ጠንክረው በተፋለሙት መንገድ መጠን፣ በደረደሩት ልዩ ልዩ ቅርጾች ዓይነት፣ እባብን ለመመገብ በዘየዱት አቅጣጫ፣ መኪናና አየር ሲያሽከረክሩ በተጋፈጧቸውና ባሸነፏቸው ጠላቶች ብዛት፣ የተለያዩ ዓይነት የፑል፣ ኳስና የካርታ ጨዋታዎችን  በመሳተፍ ያሳዩት ብልሀት ከተጠቀሙት ጊዜ አንጻር ያመጡት ውጤት እንዲሁም ለእነዚህ  ጫወታዎች በመረጥነው ፍጥነትና የውስብስብነት ደረጃ ውጤት እየተለዋወጠና እያዝናና ያወዳድረናል።
ሊዘጋጁ ነው የተባሉት መንፈሳዊ ጨዋታዎችን ጥቅማቸውን ሳስብ ደግሞ በጣም አስደስቶኛል።
ለምሳሌ ጥቂቶቹን ልግለጽ፡-
ክርስትና ፡- የሚለው ጫወታ አንድ ሰው ወደጫወታው ዕድሜውና ጾታው ተጠይቆ፣ ወንጌል ተምሮ፣ ማመኑን ሲመሰክር በጥምቀት ምሳሌ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሲሻገር፣ ቆላውንና ደጋውን አቋርጦ ተራራ ላይ ካለችው ቤ/ክ ሲደርስ፣ ደጀ ሰላሙ ላይ ሲሳለም በሩ ሲከፈትለት፣ ገብቶ ሲሰግድ ሲጸልይ ቆይቶ ወደ በሩ ሲጠጋ ጾታው ታይቶ በትክክለኛው በር ሲጠጋ ሲከፈትለት፣ ገብቶ የሚቆምበትን ቦታ አይቶ ጨዋታው ቅዳሴ መጀመሩን ያበሥራል፤

Thursday, May 17, 2012

ደብረ ዳሞ ን በአጭሩ

    
           በ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው። ደብረ ዳሞ ከአዲግራት በስተምዕራብ በመካከለኛው ትግራይ ይገኛል። ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከቆዳ በተሰራ ገመድ ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይይዛል። የተሰራውም አቡነ አረጋዊ 6ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበር ትውፊት አለ። ቶማስ ፓከናም የተባለው የታሪክ ተመራማሪ አምባው እንደ ወህኒ አምባ ግሸን ወንድ የነገስታት ዝርያወችን ለማሰሪያነት ያገለግል እንደነበር ትውፊት እንዳለ በጥናት ደርሶበታል።  የገዳሙ ውጫዊ ወለሎች በጥንቱ ዘመን ዘዴ፣ የኖራ ድንጋይንና የጥድ እንጨትን በማፈራረቅ የተሰራ ነበር። ይህም በስነ ህንፃ ጥበበ አክሱማዊ ዘዴ አሰራር ይባላል።
ደብረ ዳሞ መወጣጫ ጠፍር
እዚህ አምባ ላይ የሰውም ሆነ የእንስሳ ሴቶች መውጣት አጥብቆ የተከለከለ ነው። ሆኖም ግን በግራኝ አህመድ ወረራ ወቅት ንግስት ሰብለ ወንጌል እና ደንገጡሮቻ እዚህ አምባ ላይ በመጠለል ከሞት ድነዋል። ተራራው ላይ ምንጭና እህል የሚዘራበት ሰፊ መሬት ስለነበር ፖርቱጋሎቹ እነ ክራስታቮ ደጋማ ከአምባው ደርሰው ንግስቲቱ እንድትወርድ እስከአሳመኗት ድረስ የግራኝን ሰራዊት ከዚህ አምባ ላይ ሆና መከላከል ችላለች።
ደብረ ዳሞ አምባ ከሩቁ - ምኩራቡ በሁሉም አቅጣጫ አንድ አይነት ኩርባ ያለው የተፈጥሮ ቅጥር ነው


ደብረ ዳሞ ገዳም በጥንታዊ የህንጻ አሰራር ዘዴ-
ደብረ ዳሞ ቤተክርስቲያን

ምንጭ ፡-ውክፔድያ 

Thursday, May 10, 2012

"የበገና አገልግሎት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን"




በገና የኢትዮጵያ ቤ/ክርስቲያን የምስጋና መሳሪያ

"በገና"፡- እንደሌሎች የሃገራችን ጥልቅ ብሔራዊ የታሪክ ሃብቶችና በታሪክም ከእስራኤል ቀጥሎየኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ የሀገር ሀብት እንደመሆኑ መጠን ሁለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡

እነርሱም፡-
1. ሰዋስዋዊ ትርጉምና
2. ሥነ ቃላዊ ትርጉም.............. ይባላሉ፡፡
                                                                                              

1. የበገና ሰዋስዋዊ ትርጉም
"በገና" የሚለው ስምና "በገነ" የሚለው ግሥ በተለያዩ መዝገበ ቃላትና የቋንቋ ሊቃውንት ተተርጉሞእናገኛለን፡፡ ለምሳሌ፡- አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ"መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ"በሚል መጽሐፋቸው በሁለት መልኩ ማለት "ሲጠቅብና ሲላላ" ብለው በማመሳጠር እንዲህብለውተርጉመውታል፡፡
በገና ፡- በዕብራይስጥ ናጌን ይባላል ካሉ በኋላ ሲተረጉሙት ፡- ነዘረ፣ መታ፣ ደረደረ፣ ማለትነው፡፡ ሲጠብቅ ግን ፡- ነደደ፣ ተቆጣ... ያሰኛል ብሏል፡፡
በገና፡ - በቁሙ መዝሙር ማለት ነው ብለውም ፈትተውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ፡መጽሐፈ ስዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)
አባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የትግርኛ መዝገበ ቃላት በተባለ መጽሐፋቸው፡- በገናን በቁሙ በገናብለው ተርጉመውታል፡፡ (አባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር፣ ትግርኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት፣1948፣አሥመራ)
ከሳቴ ብርሃን ተሰማ "የአማርኛ መዝገበ ቃላት" በተሰኘ መጽሐፋቸው እንዲህ ዓይነት ትርጉምሰጥተውታል፡፡

Tuesday, May 8, 2012

አርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር


መግቢያ
ጎንደር በኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ከአክሱምና ላሊበላ ቀጥሎ ትልቋ የመንግሥት ማዕከል ነበረች፡፡ በመንግሥት ማዕከልነት የተቆረቆረችው በአፄ ፋሲል (1624-1660 ዓ.ም) ነው፡፡

ጎንደር የመንግሥት ማዕከል ብቻ ሳትሆን በጊዜው የመንፈሳዊ ትምህርት ማዕከልም ነበረች፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመጻሕፍት እና የአቋቋም ትምህርት ይበልጥ የተስፋፋውና በየሀገሩ ያሉ ሊቃውንት በመናገሻ ከተማዋ ጎንደር በነገሥታቱ አማካይነት በመሰባሰባቸው ሲሆን ከዚያን ዘመን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ መንፈሳዊ ትምህርት በስፋት የሚሰጥባት የትምህርት ማዕከል ለመሆን ችላለች፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ጎንደር በሚገኙ 21 ወረዳዎች ከ2117 ያላነሱ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ሲኖሩ በዋና ከተማዋ ደግሞ ከ92 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡

Thursday, May 3, 2012

አቡነ አብርሃምን ሳውቃቸው

http://www.danielkibret.com/2011/11/blog-post_14.html?spref=blዳንኤል ክብረት
እኔ እና አቡነ አብርሃም የምንተዋወቀው ገና ወደዚህ መዓርግ ሳይመጡ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሳይሆኑ፣ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ሲማሩ ነው፡፡ ይበልጥ ያወቅኳቸው ግን ብዙ በሠሩበት እና ማንነታቸውንም ባስመሰከሩበት በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አለቃነታቸው ነበር፡፡
የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ትምህርት ቤት ሲከፈት ከመድኃኒት ዘዋለ እና ከዳግማዊት ግርማይ ጋር የት/ቤቱ ቦርድ ሆኜ ሠርቼ ነበር፡፡ አቡነ አብርሃምን በሚገባ ያወቅኳቸው ያኔ ነው፡፡ እንደ አለቃ ይመራሉ፣ እንደ ባለሞያ ይሞግታሉ፣ እንደ አባት ይጋብዛሉ፣ እንደ ወንድም ስንጠፋ ይፈልጋሉ፣ እንደ ኃላፊ ይከታተላሉ፡፡
ትምህርት ቤቱን ለመስከረም ለማድረስ የነበረን ጊዜ ከሦስት ወር የማይበልጥ ነበር፡፡ ተማሪ መዝግበን፣ መምህር ቀጥረን፣ መዋቅር ዘርግተን፣ ቁሳቁስ አሟልተን፣ የትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ አግኝተን ለማጠናቀቅ ሦስት ወር፡፡ መቼም በቦታው እርሳቸው ባይኖሩ ኖሮ ይሳካ ነበር ብዬ ለመገመት ይቸግረኛል፡፡
ሁሌም የማደንቀው አንድ አመለካከት አላቸው የተሻለ ሃሳብ ያመጣ ያሸንፋቸዋል፡፡ በስብሰባችን ላይ እርሳቸው አስተዳዳሪ መሆናቸውን እንኳን እኛ እርሳቸው ራሳቸው አያስታውሱትም ነበር፡፡ ክርክር ነው፣ ሙግት ነው፣ የተሻለ ነገር አምጡ ነው፡፡ በመጨረሻ የተሻለ ነገር ያለው ያሸንፋል፡፡ የርሳቸውን ሃሳብ የጣልንበት ብዙ ጊዜ ነበር፡፡ አንድም ቀን ግን ቅር ብሏቸው ወይንም አለቅነታቸውን ተጠቅመው ድምፅን በድምፅ ሽረውት አያውቁም፡፡
ሌላም የሚገርመኝ ጠባይ ነበራቸው፡፡ የሚሠራ ሰው ካገኙ ሥልጣናቸውን ጭምር ለዚያ ሰው ለማስረከብ ምንም አይቆጫቸውም፡፡ የሚያምኑት ሰው የሚሠራን ሰው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሲናገሩ የምሰማው አንድ ነገር ነው፡፡ «እናንተ የምትችሉትን ሥሩ፤ ሰዎች እኔን ሲጠይቁኝ አላውቀውም እንዳልል ግን ምን እንደ ምትሠሩ ንገሩኝ፤ ብታጠፉ እኔ ኃላፊነት እወስዳለሁ»ÝÝ በዚህ አስተሳሰብ ባይሆን ኖሮ ዛሬ አፍ አውጥቶ ሥራቸውን የሚመሰክረው የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ትምህርት ቤትን መሥራት ቀርቶ ማሰብ አይቻልም ነበር፡፡

የመነኩሳት ሕይወት

http://www.eotcmbw.blogspot.com/2011/11/blog-post_15.html#more

ምንም እንኳን የድንግልናና የምናኔ ኑሮ ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም የምንኩስና መሥራችና አባት ቅዱስ እንጦንስ ነው፡፡ አባ እንጦንስ ግብፅ ውስጥ በምትገኝ ቆማ በምትባል ቦታ በ251 ዓ.ም ተወለደ፡፡ ወላጆቹ ሀብታሞችና ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ ከወላጆቹ ዕረፍት በኋላ የነበረውን ሀብት ለድሆች መጽውቶ መንኩሶ ብዙ ዓመት በብሕትውና ኖረ፡፡

በዚያን ጊዜ ብዙ ታምራትን ስለሠራ ሕዝቡ ግማሹ እሱን አይቶ ለማድነቅ የቀረው ደግሞ በእርሱ ጸሎት ለመፈወስ ወደነበረበት ቦታ ይጐርፍ ነበር፡፡ እርሱም በ356 ዓ.ም ዐረፈ፡፡

አባ ጳኩሚስ የተባለ ሌላው አባት በላይኛው ግብፅ ውስጥ ብዙ ገዳማትን በመሥራት የምንኩስናን ሕግና ሥርዓት በመወሰን ስለምንኩስና መስፋፋት ብዙ ደክሟል /290-347 ዓ.ም/፡፡ አንድ ቀን ወደ ዱር እንጨት ፍለጋ ሔዶ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት የአንድነትን ማኅበር ለመሥራት መነኮሳትን እንዲሰበስብ አዘዘው፡፡ ብዙ አማኞች እየናፈቁት ማግኘት ያልቻሉትን ገዳማዊ ሕይወት ያገኙ ዘንድ ገዳም ለመመሥረት የሚስችለውንና የሚያስተዳድርበትን በነሐስ ላይ የተቀረጸ ሕግ ሰጠው፡፡ አባ ጳኩሚስም ከመልአኩ በተሰጠው ሕግ መሠረት የሚተዳደር ገዳም አቋቋመ፡፡ ይኸውም መነኮሳቱ ጠዋትና ማታ አብረው እንዲፀልዩ በአንድነት እንዲሠሩ ገቢና ወጪያቸው አንድ ላይ እንዲሆን በአንድነት እንዲመገቡ፣ ልብሳቸው አንድ አይነት እንዲሆንና እነዚህን የመሳሰሉትን ደንቦች አወጣላቸው፡፡ በዚህ መሠረት መነኮሳቱ የዕለት ምግባቸውን የሚያገኙት እየሠሩ ነበር፡፡ ከሴቶችም የምንኩስናን ሕይወት የጀመረች የአባ ጳኩሚስ እህት ማርያም ናት፡፡

Wednesday, May 2, 2012

የሚያሸንፍ ፍቅር

ዳንኤል ክብረት    http://www.danielkibret.com/2011/05/blog-post.html?spref=fb


አንድ ሰርግ ውስጥ አንድ ሽማግሌ ሙሽሮቹን ሊመርቁ ቆሙና «አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ» ብለው ሲመርቁ ሰማሁ፡፡ እስካሁን ብዙ ሠርግ ተገኝቼ ምርቃት ሰምቻለሁ እንዲህ ያለ ምርቃት ሰምቼ አላውቅም፡፡ ምን ማለታቸው ይሆን? እያልኩ በኅሊናዬ ሳብሰለስለው ቆየሁ፡፡ ­«አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር? ደጋግሜ አሰብኩት፡፡
ይህንን ሳወጣ እና ሳወርድ እንዳጋጣሚ ሽማግሌው ምርቃታቸውን ፈጽመው እኔ የነበርኩበት ጠረጲዛ መጡና ተቀመጡ፡፡ መጠየቅ አለብኝ አልኩና አንገቴን በጠረጲዛው ላይ ሰገግ አድርጌ
«ደኅና ዋሉ አባቴ» አልኳቸው፡፡
«ይመስገነው ደኅና ነኝ» አሉኝ፡፡
«ቅድም የመረቁት ምርቃት ሰምቼው ስለማላውቅ ገረመኝ» አልኩ ወሬ ለመወጠን ብዬ፡፡
«አንተ ብቻ አይደለህም ብዙዎች ይገርማቸዋል» አሉ ፈገግ ብለው፡፡
«ምን ማለትዎ ነው ግን»
«መጀመርያ አንድ ታሪክ ልንገርህ» አሉኝ ጃኖአቸውን ወደ ቀኝ መለስ እያደረጉ፡፡ እኔም ወንበር ቀየርኩና አጠገባቸው ተደላድዬ ተቀመጥኩ፡፡
«አንድ ጊዜ አንዲት እኅት ምክር ልትጠይቀኝ መጣች፡፡ እናም እንዲህ ስትል አጫወተችኝ፡፡ እኔ እና ባለቤቴ ከተጋባን ስምንት ዓመታችን ነው ሁለት ልጆችንም ወልደናል፡፡ የራሳችን ቤት እና መኪና አለን፡፡ ሁለታችንም የየራሳችን በቂ ደመወዝ የሚገኝበት ሥራ አለን፡፡
ይህንን ያህል ዓመት በትዳር ስንኖር ተጋጭተን ወይንም ተጣልተን አናውቅም፡፡ እንኳን ለመጣላት ለመፋቀረም ጊዜ አልነበረንም፡፡ ጭቅጨቅ፣ ንዝንዝ፣ በዚህ ወጣ፣ በዚህ ወረደ የሚባል ነገር በቤታችን ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም፡፡ ጎረቤቶቻችን እና የሚያውቁን ሁሉ በኛ ይቀናሉ፡፡ እርሱን ምን የመሰለች ሚስት አለችህ ይሉታል፤ እኔንም ምን የመሰለ ባል አለሽ ይሉኛል፡፡
አንድ ጊዜ ጓደኛዬን ለማየት እና በዚያውም ለመዝናናት ብዬ ናይሮቢ ሄድኩ፡፡ ባለቤቴ ሥራ ስለነበረው አልሄደም፡፡ ጓደኛዬ ትዳር ከያዘች አምስት ዓመቷ ነው፡፡ ባለቤቷ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ስለሚሠራ ነው ኬንያ የሄዱት፡፡ እነርሱ ቤት አንድ ሳምንት ተቀመጥኩ፡፡