Saturday, April 28, 2012

ግሸን ደብረከርቤ ዳግማዊት ጎልጎታ - የግማደ መስቀሉ መገኛ



ግሸን ማርያም ደብር በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና በመቅደላ፤ በደላንታ፤ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ በርዋ አንድ ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በበርዋ ከተገባ በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡ በትግራይ እንደ ደብረ ዳሞ በበጌምድር እንደዙር አምባ በመንዝ እንደ አፍቅራ ናት ፡፡

ወደዚህች ደብር ለመሔድ በረሐ አቋርጦ በሸሎን በመሻገር ፫ ሰዓት መንገድ አቀበት በመውጣት አንድ ቀን ሙሉ ተጉዞ ማታ ፲፪ ሰዓት ይገባል ፡፡ግሸን ማርያም በፊት ደብረ እግዚአብሔር ትባል ነበር ፡፡ይህ ደብረ እግዚአብሔር የሚለው ስያሜም በጻድቁ ንጉሥ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር  አብ ስም ስለነበረ ደብረ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራ ነው፡፡ ከዚያም በዓጼ ድግናዣን ዘመን መንግሥት የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብር ነጎድጓድ ተብሎ ሲሰየም ግሸን  የሐይቅ ግዛት ስለሆነች ከደብረ እግዚአብሔር ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች ፡፡

ከዚያም በ ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓጼ ዘርአ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች የደብሩ አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ይባል ነበር፡፡ ከደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡

Wednesday, April 25, 2012

መመረሽ፣መፈረሽ፣መደንበሽ

Tuesday, April 24, 2012

ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ልጸልይ?



 ባለፈው ስለጸሎት የመለሱትን አይቼ በጣም ደስ ብሎኛል።የኔም ጥያቄ ነበር።ከዚህ ጋር ግን አብረው ቢመልሱልኝ  መልካም ነው ብዬ ጥያቄዬን ልኬአለሁ።ለመሆኑ በየእለቱ መጸለይ ያለብኝ ጸሎት የትኛው ነው?በየትኛው ሰአትስ ልጸልይ?የታዘዘዉን መጸለይ ካልቻልኩ በሥራ ምክንያት ከተቻኮልኩስ ምን ብዬ ከቤቴ ልውጣ?መልሱን በጉጉት እጠብቃለሁ።
      ኃይለ ገብርኤል   ከጀርመን
መልስ-ጸሎት በክርስትና ሕይወት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን  ባለፈው ጊዜ አይተናል፡፡በዚህ ጽሑፍ  በወንድማችን ጥያቄ መሠረት የምንጸልይባቸውን  ጊዜያት፣የምንጸልየውን  የጸሎ ዓይነት፣ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
1. የጸሎት ጊዜያት
ልበ  አምላክ ነቢየ  ልዑል ቅዱስ ዳዊት”ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ ፣ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ 118-164/ብሎ እንደተናገረ  ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ  እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.1   ጸሎተ ነግህ
ቅዱስ ዳዊትአምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁመዝ 62÷11 እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡
.ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን።
·የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡
·የሰውን  ልጅ  በመዓልትና  በሌሊት  የሚጠብቁ  መላእክት  ለተልዕኮ  ሲፋጠኑ  የሚገናኙበት  ሰዓት  ነው፡፡የሌሊቱ  መልአክ  ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡
.ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ 
እንጸልያለን።

የኔ ጀግና



የኔ ጀግና

Monday, April 23, 2012

አባ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ

http://www.melakuezezew.info/2011/07/blog-post.html
አባ ሙሴ ጸሊም በትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን አስቀድሞ በውንብድና ኑሮ ሕይወቱን ይገፋ ነበር፡፡ ሰዎች ከገድሉ የተነሳ ያደንቁታል፡፡እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበርና እርሱ በሥጋው ጠንካራ ፤ በሥራውም ኃይለኛ ነበር፡፡
አባ ሙሴ ጸሊምም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ፤ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ፡፡ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር ፡፡
                                           አባ ሙሴ ጸሊም  ኢትዮጵያዊ
በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኮሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ፤ ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው፡፡  ያንጊዜም ተነሳ ሰይፉንም ታጥቆ ወደአስቄጥስ ገዳም ሄደ ፤ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው ፤ አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ አለው ፡፡ አባ ኤስድሮስም ወደአባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው፡፡ እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲህም አለው ታግሰህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ
i am coming